TO ALL NIEMI 2016 Candidates

Dear NIEMI 2016 Candidates,

SPHMMC has a unique Policy of transparency while conducting high-stakes exams. A strong appeal system is a pillar of Transparency. Accordingly, 10 people came to have their exams checked and 8 of them were found to be candidates for the interview and one of them had the highest grade for the exam.

Most of the problems were due

  1. Coloring the wrong code and correction done with the answer key of a different code
  2. While coloring the answers instructions were not followed and the computer marked it wrong but marks were given during checking manually.

Because of the above reasons, in Discussion with all stakeholders, it was decided that an equal opportunity for all NIEMI exam candidates should be given to make the exam fair based on our transparency policy.

Therefore, all answer sheets will be marked manually and

  • ALL GRADE POSTED IS CANCELLED
  • THE INTERVIEW IS CANCELLED
  • AFTER MANUAL CORRECTION IS FINISHED THE CANDIDATES WHO WILL QUALIFY FOR THE INTERVIEW WILL BE POSTED

For all the inconvenience that you may have faced, THE SPHMM exam administration team and stakeholders would like to forward their heartfelt apology. We feel that all of you understand that this is done for the fair treatment of all examinees based on our transparency Policy for any exam administration.

ዉድ የ NIEMI 2016 ዕጩ ተወዳዳሪዎች (ተፈታኞች)

ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ  የሚሰጣቸዉን ፈተናዎች በተመለከተ እጅግ ልዩ፤ ግልጽ እና ተአማኒነትን የሚከተል የአሰራር መርህ አለዉ፡፡በዚህ መሰረት 10 ተፈታኞች በፈተናዉ ዉጤት ቅሬታ አቅርበዉ 8ቱ የቃል ፈተና ላይ ሊካተቱ ችለዋል፡፡ በአንፃሩ አንድ ተፈታኝ ለቃል ፈተናዉ ያላለፈ ነገር ግን ቅሬታ አቅርቦ በእጅ በሚታረምበት ወቅት  ከፍተኛ ዉጤት በማምጣት ወደ ቃል ፈተናዉ ተካቶአል፡፡ በዚህ ምክንያት

                                አብዛኛዉ ችግር የነበረዉ

  • ተፈታኖች የፈተናዉ ኮድ በምታጠቁሩበት ወቅት የተሳሳተ የኮድ አጠቋቆር ስለነበር፣  ፈተናው የራሱ ባልሆነ ኮድ መታረሙ
  • ተፈታኞች መልሱን በምታጠቁሩበት ወቅት የተሰጣችሁን መመሪያ በደንብ ስላልተተገበረ አንድአንዶቹ ከተሰጠው ቦታ ውጪ በማጥቆር ፣ ሎሎች በደንብ ያልተጠቆሩ ወይም በደንብ ያልጠፉትን ኮምፒውተሩ ሲያነብ የተሳሳተ ሲል ፤ በእጅ ሲታረም ግን ትክክል እንደሆነ በመቆጠሩ

ከላይ በተጠቀሰዉ ችግር ምክንያት ሁላችንም ባለድርሻ አካላት ተወያይተን የሁሉንም ተፈታኝ መብት ለማስጠበቅና የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረም ቅሬታ ላቀረቡት ብቻ ሳይሆን ሁሉም የ ’NIEMI ‘ተፈታኞች  እኩል መብት ስላላቸዉ ባለን የግልፅነት መርህ ሁሉም የመልስ መስጫ ወረቀቶች በእጅ እንዲታረሙ ተወስኗል፡፡

በዚህም መሰረት

  • ሁሉም የተለጠፉት የፈተና ዉጤቶች ተሰርዘዋል፡፡
  • የቃል ፈተናዉም ተሰርዟል፡፡

ሁሉም የፈተና ዉጤት በእጅ ከታረመ በኃላ ለቃል ፈተናዉ ብቁ የሆኑትን የስም ዝርዝር በድጋሚ በድህረ ገጽ ይለጠፋል፡፡

ለተፈጠረዉ ችግሮች እና  መንገላታት የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የፈተና ሂደት ኮሚቴ እና አጋር አካላት ልባዊ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ይህንን ያደረግነዉ ሁላችሁንም ተወዳዳሪዎች (ተፈታኞች) እኩል ለማስተናገድ ባለን የግልጽነት አሰራር መርህ በመሆኑ እንደምትረዱ በመተማመን ነዉ ፡፡

  • +251 112 75 01 25
  • info@sphmmc.edu.et
  • Gulele Sub-City, Addis Ababa, Ethiopia PO Box 1271